መግቢያ
በApril 2016 መጀመሪያ አንድ ማታ ከጥቂት ወንድሞች ጋር ሆነን በExodus TV Show (ቤተልሔም ታፈሰ) የተዘጋጀ የሐዋርያ ዘላለም (ፓዝ) ጌታቸው ተከስተን (ከዚህ በኋላ ሐዋርያ ፖዝ ወይም ፖዝ) ቃለ መጠይቅ ተመለከትን። ... በቃለ መጠይቁ ውስጥ ተጠያቂው ገሃድ ያደረጋቸው ጉልህ የስሕተት ትምህርቶች በቀላሉ መታየት የሌለባቸው መሆናቸውን ራሳቸው የሚገልጡ ናቸው።
... በጽሑፉ የማቀርበው ባገጠጡት ስሕተቶች፥ በተለይም አስተምህሮታዊ በሆኑቱና በኢየሱስ ማንነት ላይ በተቃጡቱ ላይ ብቻ ነው። ... በቃለ መጠይቁ ውስጥ ይህ ሰው ኢየሱስን አራት ነገሮች አድርጎ አሳይቶአል። እነዚህ አራት ነገሮች፥
- ፖዝ አድራጊ/አስደራጊ (ፖዝ አስደራጊው ኢየሱስ)፣
- የሰየጠነው/ሰይጣን የሆነው (ሰይጣኑ ኢየሱስ)፤
- ሰው ብቻ/ሰው ብቻው (ሰውየው ኢየሱስ)፤
- ታጃቢ (ታጃቢው ኢየሱስ)።
... 'እነዚህ እንደ ፖዝ ያሉት ሰዎች የሚናገሩት ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ ነው ወይስ እነርሱ የፈጠሩት ኢየሱስ?' ብሎ መጠየቅ ተገቢና የመልሳችን መዝገብ ወደሚገኝበት ወደ ቃሉ እንድንሄድ የሚያደርገን ጥያቄ ነው፡፡ ... ሐዋርያው ጳውሎስ በ2ቆሮ. 11፥4 "የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።" ያለው ያኔም አሁንም እውነት ነው፡፡ ሌላ ኢየሱስ፥ ልዩ መንፈስ፥ ልዩ ወንጌል። ይህ ታዲያ የሚታገሡት ትምህርት መሆን የለበትም።